02.18.2010 - By DW.COM | Deutsche Welle
አና በሞተር ሳይክል ወደ በርንአወር መንገድ ትወሰዳለች። የሚወስዳት ሰው ኤምረ ኦጉር ይባላል። መልካም ጊዜ በበርሊን ይመኝላታል። ግን ከቀይ ለባሿ ሴት ለማምለጥና የብረቱን ሳጥን ለማግኘት ይበቃት ይሆን?
ተጫዋቹ አና ጊዜ ስለሌላት ወደ በርንአወር መንገድ የሚወስዳት ሰው እንድትፈልግ ይመክራታል። አናን በሞተር ሳይክል አንድ ወጣት ሰውዬ ፤ የበኋላው መርማሪ ኤምረ ኦጉር ይወስዳታል። ከዚያም አና ሀይድሩንና ፓውልን ስታገኝ ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ፓውልና የሀይድሩን ባል ሊያባርሯት ይችላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አና ማህሌቱን ለማምጣት መንገድ ትጀምራለች። ግን ማህሌቱ ከብዙ አመታት በኋላ አሁንም እዚያው ይሆን ያለው?