Mission Europe - Mission Berlin | Учить немецкий | Deutsche Welle

Mission Berlin 09 – ያልተሟላ ጥቆማ

02.18.2010 - By DW.COM | Deutsche WellePlay

Download our free app to listen on your phone

Download on the App StoreGet it on Google Play

አና ከቲያትር ቤቱ ትጠፋለች። ግን ቀይ ለባሿ ሴት የፓውል ሱቅ እስከምትገባ ድረስ ትከታተላለች። በሀይድሩን እርዳታ አማካኝነት አና ማምለጥ ትችላለች። እንቆቅልሹን ለመፍታት ሙሉ መረጃ የላትም። የተቀረውን ከየት ታገኝ ይሆን?

መርማሪ ኦጉር አናን ከጊዜው ሽብር ፈጣሪዎች ፤ RATAVA እንድትጠነቀቅ ይነግራታል። ወደ ሰዐት መሸጫው ስንመለስ፤ ፓውል ቪንክለር የተጠገነውን የመጫወቻ ቀፎ ያሳያታል። የ ፍሪድሪክ ኦጉስት ዳህፌግ "Nostalgie" የሙዚቃ ቅንብር ትጫወታለች። "Unsere Melodie, Anna", ይላል ፓውል። ግን አና ምንም አይገባትም። በድንገት ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ተኩስ ትከፍታለች። ሀይድሩን ድራይ በቦታው ትገኝና ፓውልና አና ማምለጥ እንዲችሉ ታደርጋለች። አና አሁን ሁለት መረጃ ነጥቦች አግኝታለች። እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 እና ህዳር 9። ግን የትኛው አመት ነው?

More episodes from Mission Europe - Mission Berlin | Учить немецкий | Deutsche Welle