02.18.2010 - By DW.COM | Deutsche Welle
ኦጉር ከቀይ ለባሿ ጋር በተከፈተው የተኩስ ልውውጥ ይቆስላል። ለአናም ስለ RATAVA ታሪካዊ ክስተት ይገልፅለታል። እንደምንም ብሎ እ ኤ አ ህዳር 9 ይላታል። ግን በየትኛው አመት?
መርማሪ ኦጉር አና ቲያትር ቤት እንደተደበቀች ይገምትና እንድታመልጥ ይገፋፋታል። ቀይ ለባሿ ሴት አና ላይ ትተኩስና አና አንድ ህይወት ታጣለች። ጨዋታው እንደገና ከተጀመረ በኋላ ኦጉር ለአና ፤ በቡድን ያሉ የጊዜው ሽብር ፈጣሪዎች ታሪክ ሊቀይሩ እንደሚፈልጉ ይነግራታል። ምንም እንኳን መርማሪው በሞት አፋፍ ቢሆንም አናን ወሳኝ የሆነውን ቀን ህዳር 9 ይጠቁማታል። ግን በየትኛው አመት ማለቱ ነው?