02.18.2010 - By DW.COM | Deutsche Welle
አና የመጫወቻ ቀፎውን ለማስጠገን ሰዐት ሰሪ ጋር ትመጣለች። ለፓውል ቪንክለር ግን ነገሩ ከጥገና ትዛዝ በላይ ነው።
ፓውል ቪንክለር የመጫወቻ ቀፎውን ሲከፍት ውስጡ አንድ ወረቀት ላይ የቁጥር ቁልፍ 19610813 ያገኛል። ምን ማለት ነው? ፓውል ቪንክለር ስለ ምንድን ነው የሚያወራው? አና የመጫወቻ ቀፎውን ልጠግንልህ ትላለች። እሱ ደግሞ ከዚህ በፊት እንደሚተዋወቁ ይገምታል። በመካከልም አና ጨዋታውን መዝግባ ታስቀምጣለች። ከአሁን በኋላ 90 ደቂቃዎችና ሁለት ህይወት አሏት። ሙዚቃውን ተከትላለች ግን "In der Teilung liegt die Lösung" ምን ማለት ነው?