02.18.2010 - By DW.COM | Deutsche Welle
አና ወደ ካንት መንገድ አቅጣጫ ታመራለች። መንገድ መጠየቅ ስላለባት ሰአቷ ይባክናል። ጥቁር ኮፍያ ያደረጉ ሞተር ሳልክል ነጂዎች ይደርሱባትና ይተኩሳሉ።
ሞተር ሳልክለኞቹ አናን ፋታ አይሰጧትም። በተልዕኮዋ ላይ በተጨማሪም ይረፍድባታል። ተሽከርካሪ ጎማ ያለው ጫማ የሚሄዱትን ልጆች መንገድ ስትጠይቅ ሞተር ሳልክለኞቹ ተኩሰው ይገድሏታል። ጨዋታው በድጋሚ ከተጀመረ በኋላ በመጨረሻ ካንት መንገድ ላይ ትደርሳለች። ግን እዚያ የምትፈልገውን ታገኝ ይሆን?