02.18.2010 - By DW.COM | Deutsche Welle
አና የመርማሪውን ጥያቄ እየመለሰች ሳለ የሞተር ሳይክል ድምፅና ተኩስ ይከፈታል። አና ትጠፋለች።የመጫወቻ ቀፎ ላይ አንድ አድራሻ ታገኛለች። ይኼ እሷን ይረዳት ይሆን?
አና ከአባራሪዎቿ ወደ አንድ ሙዜም ማምለጫ አጋጣሚ ታገኛለች። ፓሊሶች ወይም ጥቁር ኮፊያ ያደረጉ ታጣቂ ሞተር ሳይክል ነጂዎች እንዳያገኝዋት ስለፈራች የወንዶች መፀዳጫ ቤት ትደበቃለች።