የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 674 ሺህ 823 ተፈታኞች ውስጥ 5.4 ከመቶ ብቻ ማለፋቸው እጅግ በጣም እንዳስደነገጣቸው እና እንዳሳዘናቸው ተማሪዎች እና መምህራን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ላለፉት ሦስት ተከታታይ አመታት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት የቻሉት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ በተማሪዎቹ የወደፊት እጣ ፈንታ እና በሀገሪቱ ላይ የሚፈጥረው ጫና እጅግ እንደሚያሳስባቸውም ገልጸዋል።