መጽሐፈ ሳሙኤል የሦስት ሰዎችን የሕይወት ታሪክ በአጭሩ በመዘገብ ስለእግዚአብሔርን እውነት ይነግረናል፡፡ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት፡- ሳሙኤል፣ ሳኦልና ዳዊት እንዲሁም በእነርሱ ላይ የሆነው ነገር ሁሉ ለእኛ ማስጠንቀቂያና ምሣሌ ናቸው፡፡ እሥራኤል በታሪኳ ከነበሯት ነገሥታት ሁሉ ዳዊት ምርጡ ንጉሥ ነበር፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ትክክለኛ ፍርድን ይፈርድ የነበረ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም አስፈላጊ