ምንም እንኳን ዳዊት በስነ ምግባርና በመንፈሳዊ ነገር ቢወድቅም እግዚአብሔር ነፍሱንና መንግሥቱን አደሰለት፡፡ ዳዊት የተለማመደው የእግዚአብሔር በረከት የሆነው ይቅርታና ተሐድሶ ወደ ሕይወቱ የመጣው እርሱ ኃጢአቱን በመናዘዝና ንሥሃ በመግባት በጌታ መንገድ ለመሄድ በመወሰኑ ነው፡፡ ልክ እንደ ዳዊት እኛም የበደለኝነት ስሜት ችግር አለብን፡፡ ለዚህ የበደለኝነት ስሜት ችግር የእግዚአብሔር ይቅርታ መፍትሔ ነው