Sost kilo

ቻው ፡ ቻው | ጉራማይሌ መፅሐፍ


Listen Later

እንደዛ ነው የሚያደርጉት ፤ ይሄዳሉ ። ምንም ሳይሉህ ይሄዳሉ ። እንደጨረቃ ሙላታቸው ይጎድላል - ይገምሳል - ይቀጥኑ ይቀጥኑና - በሆነ ቀን ቀና ስትል የሉም ። ለመከተያ እንኳ ዳና ሳይተውልህ - ልክ እንደ ወቅቶች ፤ እንዳምናዎች ፤ እንደትናንቶች ... ሄድን ሳይሉ ፥ ፍውው …!
በዳ'ባድመ መሐል ጥለውህ ሄደውም እንዳልረሣሀቸው ማወቅ ይፈልጋሉ ። ይሄ መሻት እያደር ሲሞረሙራቸው ረፈዶ ከባቸ በኋላ 'ቻው' ይሉሃል ። ከሄዱ ከምናምን አመታት በኋላ አተኩሰው ይሰናበቱሃል ። ደሞ ቻው ሲሉህ . . .
ቻው፡ቻው !
ያንተው ሃና ።
…የደብዳቤው 31ኛ መስመር መቋጫ ላይ።
ጠርዙን ቴምብር ካሽቆጠቆጠው ቅድ ፖስታ ውስጥ ለመጨረሻ ግዜ አውጥቼ እያነበብኩት ነው ። ስድስቴም ሳነበው በዛው ክልትው ብዬ እንዳልቀር የሞትሞቴን እየተንቀጠቀጥኩ ።
የተፃፉት ሆሄያት በህላዌዬ ላይ የተደገኑ ስድር ቀልሃዎች ናቸው ። በየ'አራት ነጥቡ ባለ እረፍት የዳደረ ጠባሳዬ እንደአዲስ ቁስል ይገሸለጣል ። ፊደላቱ ከእያንዳንዷ የመስመር አፎት እየተተኮሱ ደህና የነበርኩትን ሰውዬ በሳሱኝ ። ሽንቁር ልቤን በመዳፌ እንዳፈንኩ ለአንዴና መጨረሻ ግዜ የሠላሳንም መስመር ዝናር አረገፍኩ ።
አንብቤ እንደጨረስኩ ርዶ የሚቀጠቀጥ እጄን አየሁት ። በመሃል ጣቴና ቀለበት ጣቴ መሃል በቄንጥ የያዝኩት ሲጃራዬ ቅርጣን ተሸክሟል ። ምኔ ቀድሼ ምኔ እንደማግኲት እንጃ እያለቀ ነው ። ሙት አመዱን አራግፌ መልሼ አጋምኩና አንብቤ የወጣሁትን ደብዳቤ ለኮስኩበት ። የድንገቴ ድፍረቴን ታዝቦ ነው መሰለኝ እንባዬ እንደዥረት ተንፎለፎለ ። መንሰቅሰቅ የለ አፍንጫ መምጠጥ ፤ ስቅታ የለው አይን ማበስ …ያለንጥቀት ፈሰሰ ።
[…ጭልጥ … በሐሳብ …ጭልጥ በእሣት ውስጥ ]
የሚነደው ሉክ የተበሳበትን ቅርፅ ይዞ እየሰፋ ሲቀጣጠል ቁሪ ሲጃራዬን ከእጄ አሸቀነጠርኳት ። ነበልባሉ መሀሉን አጥቁሮ እየቀላ ይነዳል ። ወላፈን ተከትሎት ቀስ ብሎ እየሻረ ወደላይ ተውለበለበ ። ክርር ያለ እሳት እንደሚሆነው አንዴ ሰማያዊ ደሞ ቀይ እየሆነ ። ንዳጁ ሲንቦገቦግ ፊቴና ከባቢው ላይ ብርሃን በብራ ይመላለሳል ።
በፊት …ሐኒን ሳቅፋት መሃላችን ከእቶን ይግል ነበር ። ቁጭ ብለን የምፈልገው ሁሉ ይሆናል። አለም እጆቼ ውስጥ ነበረች - ውጪው ብዙም አያጓጓኝም ። እየቆየሁ ግን ከማፍቀር ይልቅ የአጣታለው ስጋት ነብሰስጋዬን ያሟጠኝ ገባ ። አንድ ቀን እንደምንጋባ ሳይሆን በሆነ ለሊት ጥላኝ እንደምትሔድ አስብ ጀመር ። አጠገቤ ሆና የአሁንን ሁነት ከመቅመስ እንዳትሄድብኝ በመፍራት እፍኝ ግዜዬ አለፈ ።
ሄደችም ። ጥላኝ በሄደች ባመቱ ችፍችግ ፀጉሬ ሰየበ ። ትካዜ በነብሴ ሁሉም ማዕዘናት ደራ ። በግኑዝ መብሰልሰል የለት ማዕዴ ሆነ ። ወዴትም እንዳልራመድ ትዝታዎች ቅናዋት ሆነው ተቸነካከሩብኝ ። እንደፎቶ አንድ ቦታ ተስቅዬ ቀረሁ ። ከዚያ ወዲህ ያለው ውሏዳሬ አመት በመቁጠር ላይ ተመሰረተ።
በአንዱ ቀን ከፀሀይዋ ጋር አብራ የምትወጣ እየመሰለኝ አምሽቼ ተኝቼ ማልጄ እነሳለሁ ። ብዙ ያልታዩ ቲያትሮችን በአይምሮዬ እደርስ ጀመር ። ስልኬ በጠራ ቁጥር ሰርክ እደነግጣለው ። ' እሷ ብቶንስ' የሚል የናፍቆት ስቅቃት ገደለኝ ። ትመጣ ይሆን …አስፋልት ስሻገር አገኛት ይሆን … የምሯን ነው … በማይመለሱ ጥያቄዎች ሙት ልጇን እንዳልቀበረች እናት ሩሄን ስፋቅ ኖርኩ ።
[…ጭልጥ … በእሣት …ጭልጥ በሐሳብ ውስጥ ]
የሉኩን ጩኸት ሰማሁት ጠ'ጠ'ጣ'ጣ ። ጩኸቱን ስሰማ አሳዘነኝ ። በምንተዳው እንደኔ ይቃጠል ።እጄ ላይ እስኪደርስ አቆይቼው ጣቴን ከመለብለቡ በፊት ጣልኩት ።አየር ላይ ሁለቴ ቀዝፎ የወለሉ ሸካክላ (*ceramic) ላይ አረፈ ።
እሳቱ እያንዳንዷን መስመር እያጠፋ ወደ ላይ ወጣ ፤ እኔም እሱን ነበር የፈለኩት እያንዷዷን የትዝታ መስመር ማክሰም ። እሳት እንደውሃ አይደለም ሲያሻው ወደላይ ይነዳል ።እንዲ ወደኋላ ሄዶም የነበረን እንዳልነበር ያደርጋል ።
ነዶ-ነዶ የፀለመው ለብቻው ተፈረከሰ ። ፍርካሹን በጫማዬ ፊት ሶል አመድ እስኪሆን አሸሁት ። ቃላት ከወረቀቱ በነው እንደጠፉት ከጭንቅላቴ ይደመሰስ ይመስል ።
እምባዬ እንዳልቆመ -አሁንም እየወረደ መሆኑን ያወኩት ሸንጎበቴን (* ከንፈር ስር የተሸጎጠ ሪዝ) አርሶ የከሰለው ወረቀት ላይ ጠብ ሲል ሳይ ነው ።
ሁሌም ልረሳት ሳኮቦኩብ ከየት መጣች ሳትባል ፊቴ ትደቀናለች ፤ ድምቅ ጥርት ብላ ። ኖራው እንደረገፈ ግድግዳ ቅርጿ ገጦ ይወጣል ። እንዳልረሳኋትና ውኔ ሆን ብሎ እንደሚያደበዝዛት የማውቀው ይሄኔ ነው … ቀለሟኗ ሽታዋ ሳቋን ተከትለው ከች-ከተፍ ሲሉ ።
ልቤ እንደሆነ ሲበዛ ደደብ ነው ። ጭንቅላቴ ድሮ ድሮ የተገለጠለትን ዛሬም ድረስ ማመን ቸግሮታል። የገዛ ራስን እንደማሳመን ምን የሚከብድ ነገር አለ በሚካዔል?
የዛሬ መጨረሻችንን ብጠላም የምወቅሰው ግን መጀመሪያችንን ነበር ። ምናል ቀደም ባላውቃት እላለሁ ። ከሁለቱ ውጪ በመሀል የነበረን ሁሉ አይፀፅትም ። ህይወቴ እዚች የማትፀፅተው ወፍራም ነጥብ ላይ ነበር ታትማ የቀረችው ።
ወላፈኑ የደብዳቤው ቀይና ሰማያዊ ሽልም ላይ በርዶ ጠፋ ። ክሳዪ ጤሰ ።ሲጨስ ጠረኑ ከረገጥኩት ሲጋራ ጋር ተደምሮ በረንዳው ታወደ ። ሽታዋ በሱ ውስጥ ያለ መሰለኝ ። ፅርኒኗ ከልብሶቿ ኮሌታ ላይ አይጠፋም ነበር ። የአንገቷን ላቦት በወረቀቱ እንዳበሰች ሁሉ አሁንም ሽቱዋ አፍንጫዬ ገባ ።… ሳብኩት ።
…አሁን የማግኩሽን ልክ ብተነፍስሽ እረሳሻለሁ ። እወድሻለሁ ያልኩሽን ግዜ ልክ ቆጥሬ አልወድሽም ብልሽ ትወጪኛለሽ ። ሁሉንም ብሞክር ይሆናል . . . ? እኔንጃ አይመስለኝም ።
[ ለጤናህ እነደምን አለህ ? እኔ ካንተ ሀሳብና ናፍቆት . . . ] አለቺኝ በደማቅ ፅሁፍ ። የእጅ ፅሁፏን አውቀዋለው ጣቶቿን ተጭና ነው የምታቀልመው ።
በህይወት ዘመናችን ደብዳቤ ተፃፅፈን አናውቅም ። ደብዳቤ ህግና መስመር አለው ። . . [ውድ ጌታቸው] ብላ ጀመረች ፤ ብላኝ የማታውቀውን ። [እኔ እጅጉን ደህና ነኝ] …ምናምን ። ደብዳቤ አንቀፅ የወቀረው አራት መዐዘን ነው ። ፍቅራችን ህግም ቅርፅም አልነበረውም ፤ ፍሬም አልባ ነበርን ።
በአዘቅትም ውስጥ ሆኜ [ውድ ጌታቸው] ማለቷ ፈገግ እንድል ያደርገኛል ። የሀድራዬ (*mood) መለዋወጫ ቁልፍ በእጇ ነው ። ቁልፌን ካስረከብኩ በኋላ የውቃቤዋ ጋን ሆኛለሁ ። እንዳሻት ታደርገኛለች ።
ሀተታው እኔን ማፍቀር እንዳልተወች ይናገራል ። እኔ ግን በገሚሶት የምፈቀር አይደለሁም ። ወይ አልነበርኩም ። እንደኔ በቅስበት ሰባቴ ሲናፍቅ ለኖረ ሰው በገሚስ አፈቅርሃለው መባል ቅሌት ነው ።
[…ጭልጥ …ጭልጥ … በሐሳብ ውስጥ ]
እውነት ለመናገር ብዙ አልጠበኳትም ። እንደአጀማመሬ ብጠብቅሽማ ይሄ ደብዳቤም አይደርሰኝ ነበር ። አንደኛሽን በነብስ እንገናኝ ይሆናል እንጂ ።
ራሴን ጎዳሁ ። ላክምመውም ብዙ ጣርኩ ፤ አልሆነልኝም ። ትንሽ ሳገግም መዶሻ ይዘሽ ትከተክተቺኛለሽ ። ለቅስም አጥሚት በሌለበት አገር ከተሸረፈ ልብ የተሰበረ አጥንት ማከም ይቀላል ።
ትዳር ያዝኩ ።ሌላ የማላውቃትን ሴት ሚስት አድርጌ አገባሁ ። ነዳይ ምን ቢያብድ ስልቻውን አይጥልም እንዲሉ የእናቴን ጭቅጭቅ (ልጄን ምን አዚም አስነኩብኝ ብላ ስታለቅስ ) በሽሽት አገባሁ።
ሚስቴ ጥሩ
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

Sost kiloBy Leoul Zewelde

  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8

4.8

6 ratings