KALANDRAS

EPISODE 7 : ኢትዮጵያዊነት / Being Ethiopian?


Listen Later

ኢትዮጵያዊነት ማለት ምንድነው?

የኢትዮጵያዊነት ፍቺ ወይም ትርጓሜ እንደያንዳንዳችን የህይወት ትርጓሜና ተሞክሮ የሚወሰን ነው። 

አንድ መንገድ ላይ ሊስትሮ እየጠረገ ህይወቱን የሚመራ ልጅ፣ በወሲብ ንግድ የምትኖር አንድ የቡና ቤት ሴት ፣ ስልጣን ላይ ያለ የተመቸው ባለጊዜ ፣ የሃገሩን ዳር ድንበር ለማስከበር ድንበርና ተጋድሎ ላይ ያለ የሃገር ወታደር ፣ የሚጠጣው ውሃ ማግኘት ታላቅ የህይወት ፈተና የሆነበት አንድ አርብቶ አደር ፣ የዝናቡን መዘግየት እያሰበ የጎተራው ባዶነት የሚያስጨንቀው ምስኪን ገበሬ ፣ ለሃገሬ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ በማለቱ ከወህኒ የተጣለው ጋዜጠኝ ፣ የታክሲ የሚከፍለው ገንዘብ በማጣቱ በቀን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በእግሩ እየተጓዘ የሚያስተምረው መምህር ፣ መሪ ነኝ ብለው ገዢ የሆኑና ዘውዱን የጨበጡ እለት ቃላቸውን ቅርጥፍ አድርገው የበሉ ጥጋበኞች በፈጠሩት ጸብ ህይወቱ እየተመሰቃቀለ ያለ የአንድ አካባቢ ህዝብ . . . 


እነዚህ ሁሉ እንደጉራማይሌነታቸው ኢትዮጵያዊነትን የሚረዱበት መንገድም ብዙዎቻችን እንግዳ ተቀባይ ፣ የሰው ዘር መገኛ ፣ ሃይማኖተኛ ፣ ወ.ዘ.ተ . . . ከምንለው በእጅጉ የተለየ ነው።

የዚህ የፖድካስት ክፍል አላማም መስማማት ላይ እንድንደርስ ወይም ለቃሉ ፍቺ የሚሆን ሃሳብ ላይ ተስማምተን እንድንለያይ ሳይሆን እስከዛሬ ይዘን የመጣነውን እውነት እንድንሞግትና የውስጥ ጥያቄዎቻችንን አውጥተን እንድንወያይበት ታሳቢ በማድረግ የቀረበ ነው:: 

ሃሳብ አስተያየታችሁን ላኩልን።

Follow us on INSTAGRAM and TELEGRAM

...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

KALANDRASBy ካላንድራስ