አባት ሆይ … !
ፀልዬ አላውቅም - ብዙ እንዳትታዘበኝ ፤
ዛሬን ብቻ… ጆሮ ዳባ ሳትል …
ለሥጋዬ ውሉድ ፥ አንዲት ማቲ ዋጀኝ ።
'ሴት' ሆና የማምናት ፤
ካለ ሚስት አለናት ፥ አባት 'ምሆናት ።
አንዲት ልዕልት ማቲ
ሳይጋሩኝ የምወዳት - ሳትጋራ የምትወደኝ
አቤቱ - በረቂዮትህ ዋጀኝ ።
ጡት ብነሳ እንደማልጋ ላም
ባላግት ፥
ወተት ባላደማም
ጀባ'ኝ እንጂ ፥
እንደ'ዶሮ ጭሬ አፀድቃታለው
ህይወቴ የሷ መንግስት ነው ።
አባት ሆይ …
ፀልዬ አላውቅም - ብዙ እንዳትታዘበኝ ፤
ዛሬን ብቻ… ጆሮ ዳባ ሳትል …
ለሥጋዬ ውሉድ ፥ አንዲት ማቲ ዋጀኝ ።