Sost kilo

It's Christmas •••


Listen Later

ፅድ አናት ላይ - ሽልም የኮኮብ ዕድ ሳይ - በዝንፍንፍ ቅርንጫፍ የተጥመለመለ ሲባጎ ብልጭ - ድርግም ሲል - የአበርክቶ ሙዳይ ዙሪያው ሲከመር - ዜማ ሲናኝ ፥
በዓመቱ ኦሜጋ ሁሉም ወደልጅነቱ ሲሰበሰብ - በቀለም ያሸበረቁ ህፃናት ተሰብስበው ሲዘምሩ - ኩርሽም ከረሜላዎች አፋቸው ላይ እየሟሟ ሲወልል - ሞሳነት ፍፅምና መሆኑን አምነው ፥ አዛውንቶች በልጆች ሲመረቁ ፥
የበረዶ ጥጥ ብናኞችን አሳበው መላዕክት ሰብ'ን ሲስሙ - የከተማው ካቴድራሎች ስንጉሱ ብስራት ሲደውሉ - የተነጠፉ መንገዶች ሁሉ - ወደቤት አቅጣጫ ሲወስዱ - በብልቃጥ የነበረ መንፈስ ሲተን - ተኖ ቤት ሲሞላ ፥
ብርቅርቅ ኳሶች እየተብረቀረቁ ሲወዛወዙ - ቀያይ ሻማ ዎች ተለኩሰው ሲታወድ - በቁር ቆፈን ውስጥ የነበሩ ጉንጮች መልሰው ሲፈግጉ - ቤተሰብ የታከበላቸው እናቶች አይን - እንደታጠበ ብርጭቆ ሲብለጨልጭ - ሳቆች ተርፈው ወለል ላይ ሲወዳድቁ ፥
በክፍት ልቦች ውስጥ የገባ ንዝረት መልሶ ሲፈስ - ፍልቅልቅ ብላቴኖች ጌታ እንዳየ ውሻ ከግድግዳ ግድግዳ ሲዘሉ ። ነገ ጠዋት - ጦማራቸውን አንብቦ የሚመጣውን ሽማግሌ በተስፋ ሲጠብቁ ፥
ቃጭል ያነገቱ አጋዘኖችን በየብስ ሠረገላ ሲጋልቡ - በራማ ጋሪ ሲከንፉ - ጆንያ ተሸካሚው ሽማግሌ ነጭ ሪዙን እየፈተለ ሲደውል - ቦቲውን እያማታ - በየአጥቢያው ሆ'ሆይ ሲል ፥
ከአንቺ መሆን እመኛለሁ ። አድማስ ተሻግሮ የተኛ ልቤ ቀኑ ሲደርስ ይቀሰቀሳል ። አይኔን ውኃ ይሞላል ። ደሞ ፥ ደሞ መጣ ...
Prompt : Carla Thomas - It's Christmas.
It's been a long long time ,
Cant' explain why you crossed my mind
I guess it's just to wish you a merry Christmas.
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

Sost kiloBy Leoul Zewelde

  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8

4.8

6 ratings