ኢየሱስ “እኔ ማን ነኝ?” በማለት ጠየቀ፤ ጴጥሮስ በበኩሉ “አንተ ክርስቶስ ነህ!” ብሎ መለሰለት፤ ይህ ማለት ይመጣል ተብሎ ቃል የተገባው መሢሁ ነህ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አብ ኢየሱስን ለጴጥሮስ ገልጦለታል፡፡ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያኑን እየገነባ ያለው እንደ ጴጥሮስ አይነቱ ተራ ሰዎች በሚመሰክሩት ተዓምራዊ በሆነ አስደናቂ ቃል ነው፡፡ በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን የተሞላችው ተራ የሆኑ ነገር ግን አስ