Radio D | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

ክፍል 24 - የ ሀንቡርግ ጋዜጣ


Listen Later

ጉጉት ኡላሊያ ጋዜጠኞቹን ወደ ትክክለኛው መስመር ትመራቸዋለች። እነሱም የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር ይደርሱበታል። ፊሊፕ የሚያደርገውም አስተያየት ፓውላ ትደነግጣለች።
የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች አውቀው ባህር ዳር ታየ የተባለውን የአሳ ነባሪ ታሪክ ፈጥረው እንደፃፉ ፓውላ ፣ ፊሊፕና ኡላሊያ ይደርሱበታል። ይህንንም ያደረጉት የአንባቢያቸውን ቁጥር ለመጨመር ሲሉ ነው። በኋላም ፊሊፕና ፓውላ በሆነ በአንድ ቃል አጠቃቀም ይጣላሉ። ፊሊፕም ፓውላ እንድትረጋጋ ሲል የወደቡ እንኳን ደህና መጡ መቀበያ ጋር ይጋብዛታል።
ፊሊፕ ለሚለው ነገር ተጠንቅቆ ቢሆን ኖሮ ፓውላን ባላስቆጣት ነበር። በተረፈ የሚነጠሉ ግሶችን እናያለን። አንዳንድ የግስ ተሳቢዎች የግሱን ትርጉም የበለጠ ያብራራሉ። አልፎ አልፎም ግሱን ከተሳቢው ነጥሎ በቅድመ ቃል መልክ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ምዕራፉ ይመለከታል።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

Radio D | ጀርመንኛ መማር | Deutsche WelleBy DW.COM | Deutsche Welle