Sost kilo

ለመውደቅ ግን ተሥፋ አለኝ •


Listen Later

አንድ ልጇ ዱርዬ ሆኖ እንዳሸነፋት እናት … በካር ማህፀኗ ሌላ ዘር ሳይዝ … እሱኑ ስትል አሳድጋ… ሲያፄም ግዜ ከእጇ እንደወጣ… ደምላቧ ከንትቶ የምትኖርለት ሌላ ምክንያት እንዳጣች …
ብዙ ብዙ ሄዶ እግዜርን ከቦታው እንዳጣ ቄስ … እድሜውን ሙሉ የቀራቸው መፃህፍት እርባን እንዳጡበት … ረፍዶ ከመመለስና ፣ ተሳስቶም ከመሄድ ምርጫ እንዳጣ … በሁለት የቂጡ ጉንጮች ሁለት ወንበር ላይ እንደተቀመጠ …
… ተሥፋ አጥቻለው …
አሳዳሪው አረጀህ ብሎ እንዳባረረው ውሻ ። እድሜ ዘመኑን በሳጥን ታጥሮ ኖሮ … ከግቢው ሲወጣ አቅም ከድቶት ቁጊያም እንደሆነ … የሰፈር ውሾች ሊነክሱ እንደሚያሳዱት …
እድሜ ይፍታህ ታስሮ ድንገት በአመክሮ እንደማሩት ታራሚ … የሚሄድበት እንዳጣ… ከሰላሳ ዓመት በፊት ከሚያውቀው አገር መግባባት እንዳቃተው … መፈታት መታሰር እንደሆነበት …ወህኒ መመለስ እንዳማረው …
… ተሥፋ አጥቻለው …
… እና አልረካ ፥ የሚያረካኝ ነገር ጠፍቷል ። አልቀል ነገር ልጅነቴን ርቄዋለው … እንዳልተልም እምነቴ ባዶ ነው … በእንዲህ ራሴን የሀሰት ከመደገፍ የሃቅ መንሸራተቱ ይሻላል … ታኮዬን አንሱልኝ ፥ ተሥፋ ባጣም እንደምወድቅ ተሥፋ ላድርግ ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

Sost kiloBy Leoul Zewelde

  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8

4.8

6 ratings