ከትናንት ወዲያ ማታ ለት እናቴ እሪሪ ብላ እያለቀሰች ገረፈቺኝ ፤ እያነቡ እስክስታ ነገር ። ከደቂቃ በፊት ( ደብተሬ
ላይ ጭረት እስካይና እስክጠይቃት) አገር ጎረቤት ሰላም ነው ብለን ስለ ሙሉ ቁጥሮች ተካፋይ ስታስረዳኝ ነበር ። ድንገት
ተነስታ ጫማዋን አውልቃ አናት አናቴን እየጠፈጠች < ኧረ ሰዎች አቃተኝ ምናባቴ ላርገው ? > ብላ ለአገላጋዮቼ
ታሳጣኛለች ፤ ሁለተኛ በደል ። ባህሪዋ ለማንም ግራ የሚገባ አይነት ነው ። እስኪ ልፈትናት ብዬ ሁለት ቀን የሚያስቅ
ቀልድ ባወራት ራሱ ትንሽ ፈገግ ሳትል ወደ ጠብደል ምክር ትለውጠዋለች ። ምክሯ ከመብዛቱ የተነሳ አንዳንዴ እንዲሁ <
ዛሬ አመክሪኝም ኣ ? > እላታለው ። በራሷ ስቃ ትንሽ ትቆይና < እናት ላይ እንዲ ማሾፍ ጥሩ ነው ? > ብላ
ትጀምራለች . . . ሃሃሃ ..........