የሚክያስ መጽሐፍ ሦስት ታላላቅ ስብከቶችን ይዟል፡፡ ይህ ነቢይ ገበሬ ሲሆን በእስራኤልና በይሁዳ ዋና ከተሞች ለሚኖሩ የፖለቲካና የመንፈሳዊ መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰብክ ተጠራ፡፡ ሚክያስ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ስላለው ስነምግባራዊና መንፈሳዊ ብልሽቶች መሪዎችን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ ሚክያስ ሕዝቡ ከዚህ ውድቅት የሚድኑበት ብቸኛ መንገድ እግዚአብሔር ፍፁም የሆነ መሪ እርሱም መሢሁን ሲልክላቸ