ኢየሱስ “ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” አለ፡፡ ከኢየሱስ ትምህርቶች ይህን ጥቅስ ለመተርጎምም ሆነ ለመተግበር እጅግ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ እነዚህ ቃላት የሚያስተምሩት ትምህርት አለም ሰምታው የማታውቀውን ከፍተኛ ሥነ ምግባር ነው፡፡ ባለንጀራችንን እንዲሁም ጠላቶቻችንን መውደድ በእግዚአብሔር መሥፈርት የማይቻል ነው፣ ነገር ግን ይህንን ኢየሱስ በውስጣቸው ያለ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት ይችላሉ፡፡ ኢየሱስ ይህንን ሃሳብ በደጉ ሳምራዊ ታሪክ ምሳሌነት አስተማረ፡፡