በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የተወሰኑ መንፈሳዊ ሥነ ስርዓቶችንና እሴቶችን እንዲከተሏቸው ሲያሳስባቸው እንመለከታለን፡፡ የእርሱ መፍትሄ አካል ለመሆን ለሚፈልጉ ሰዎች ኢየሱስ ያስተማረው የመጀመሪያው መንፈሳዊ ሥነ ስርዓት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መጋቢነት -- እኛ ያለንና እኛ ራሳችን የእግዚአብሔር ስለሆንን እኛ የእርሱ ንብረት አስተዳዳሪዎች ነን፡፡ እግዚአብሔር በግልና በፍላጎት በምስጢር የሚሰጡ ሰዎችን በግልጽ ይሸልማል፡፡ ይህ ማለት መጋቢነት ከሰዎች ትኩረትን ለማግኘት የምናደርገው አገልግሎት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ስንል የምናደርገው አገልግሎት ነው፡፡