ደቀ መዛሙርት እና ፆም - ልክ እንደ መስጠትና ፀሎት፣ ፆም መፆም ያለበት በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ነው እንጂ የሌሎችን ትኩረት ለመሳብ መሆን የለበትም፡፡ ልክ እንደሌሎቹ ተግባራት እግዚአብሔር እርሱ የሚመለከተውን ነገር ይሸልማል፣ ያም የልባችን ፍላጎቶች ነው፡፡ መስጠት ለእግዚአብሔር ያለንን መሰጠት የምናሳይበትን እድል እንደሚሰጠን ሁሉ፣ ፆምም በሕይወታችን ውስጥ ከሥጋዊ ጉዳዮች ይልቅ ለመንፈሳዊ ነገሮች ምን ያህል ዋጋ እንደምንሰጥ የምንለካበትን እድል ይሰጠናል፡፡ ፆም የእኛ ፀሎት ምን ያህል ከልብ እንደሆነ ያሳያል፡፡