“እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ … ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” ይህ ምዕራፍ ስለ ስጋት ምን ማድረግ እንዳለብን ይናገራል፣ ነገር ግን የምዕራፉ ዋና አስተምህሮ ቅድሚያ ልንሰጣቸው ስለሚገባ ነገሮች የሚያስተምር ነው፡፡ እኛ ስንጨነቅ፣ ለምን ዓይነት ነገር ዋጋ እንደምንሰጥና ለእኛ የሚጠነቀቀውን እግዚአብሔርን ምን ያህል እንደምንታመን እያሳየን ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ ከሰጠነው፣ ሌሎች ነገሮች በልባችን ውስጥ ትክክለኛውን ሥፍራ ይይዛሉ፡፡