Sost kilo

•••ሥትናፍቂኝ


Listen Later

ስ ት ና ፍ ቂ ኝ
[ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ]
ስትናፍቂኝ …
ባሏ ለዕድሜ ይፍታሕ ወህኒ እንደተወረወረባት ሴት ነው ። መልሳ ላታገኘው ነገር እሁድን እየጠበቀች እንደምትጠይቀው …
ስትናፍቂኝ …
ሲዖል ተኮራምቶ ገነትን እንደሚያልም ሠይጣን ነው ። ምህረት ሱሚ ሆኖበት በልቡ ማብከሪያ እንደሚለምን ። ጥፍሮቹን ቢከረክም'ም ርህራሄ ተነፍጎት ምናልባትን እንደያዘ…
ስትናፍቂኝ …
በምናብሽ የሚሄድ አስፋልት ሣይና በዛ ላይ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዝ ከንቱ ደሞ አስቢ ። እየሄደ የሚመስለው ግን አንድ ቦታ ላይ እንደቆመ ። ኃይሉ ሲሟጥ አስፋልቱ በራሱ አቅጣጫ እያንደባለለ እንደሚወስደው …
ስትናፍቂኝ …
ወደቀኝ እንደሚዞር ሽክርክር ሰዓት ነው ። የግዜ ጠለል ወደኋላ እንደሚነዳው ። ነገ የሚባል ነገርን እንደማያውቅ ። ትላንትን ሲገረብ እንደሚኖር…በዕስብታ …በትውስታ … በትዝታ …
ስትናፍቂኝ …
ጠምላይ ቅጠሎቿ ረግፈው ምግቧን በምን እንደምታዘጋጅ ግራ እንደገባት ሐረግ ነው ። ፎቶሲንተሲስ ቅንጦት ሆኖባት እግሯ መጠውለግ እንደጀመረ ። ፀሐይ ግልጥ ብላላት ደመንሚን እንደወረሳት …
ስትናፍቂኝ …
እግር ከወርች በወፍጮ ድንጋይ ተቋጥሮ በቀላይ እንደተጣለ ፍርደኛ ነው ። ቁልቁል ወደወለል እየሰመጠ አየር እንደሚያቡለቀልቅ ። ወደውስጥ መተንፈስ ተዓብ እንደሆነበት …
ስትናፍቂኝ …
ብሶል ( *ኮምፓስ )ሳይዝ እንደወጣ አሳሽ ነው ። ሁሌም ሰሜኑን እንደሚስት ። አቅጣጫ ሳይኖረው ዝምብሎ እንደሚሮጥ …
ስትናፍቂኝ …
በማማሰያ ተንጠፍጥፎ ቡሖን እንደሚለቁጥ አብሲት ነው ። ውሃ ሲያቀር ከርሞ የሊጥ ባህር ውስጥ ጭልጥ ብሎ እንደሚስጥም …
ስትናፍቂኝ- እንደዛ ነው ። " ስትናፍቂኝ " እያልኩ የፃፍኩት ስናፍቅሽ ላለማለት ነው ። በኔ ማስታወስ ውስጥ መረሳት የሚባልን ኩሸት ማሰብ ሕማም ነው ። በስትናፍቂኝ ውስጥ ትናንፍቀኝ ይሆን ? የሚል ተሥፋ አለ ። አልዋሽሽም ትናፍቂኛለሽ ! ማለቴ እናፍቅሻለው … እየሄድኩ … እንደማንገናኝ እያሰብኩ … በዋልሴ ካራ ውስጤን እያጨድኩ ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

Sost kiloBy Leoul Zewelde

  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8

4.8

6 ratings