ብጹዓን ናችሁ ከሚለው አስተምህሮ ቀጥሎ ባለው የምንባብ ክፍል ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በዙሪያቸው ያለውን ሁሉ እንዲመለከቱ ካደረገ በኋላ ይህንን የተማሩትን ትምህርት ከሰው ሁሉ ጋር ባላቸው ግንኙነት የሚጠሉዋቸውን ጨምሮ በመውደድ በተግባር እንዲፈጽሙት ሲያዛቸው እናያለን፡፡ በምዕራፍ 6 ኢየሱስ ለተከታዮቹ እውነተኛ ደቀ መዝሙር ሊኖረው ስለሚገባ መንፈሳዊ ሥነ ምግባርና እሴቶች እንዲያስተውሉ ያስተምራቸዋል፡