ኦሪት ዘኁልቁ በኃይለኛ ዘይቤአዊ አነጋገሮችና ምሳሌዎች የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የምንመለከተው ነገር የሰው የመምረጥ ነፃነት ምን ያህል የእግዚአብሔርን ኃይል እንደሚገድበው ነው፡፡ ለማመን ፈቃደኛ ብንሆንና እግዚአብሔር ለእኛ ያለው መልካምና ፍጹም የሆነውን የእርሱን በረከት ለመቀበል ዝግጁ ከሆንን እርሱ ተስፋ ወደ ተገባልን መንፈሳዊ አገር ይመራናል፡፡ በእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ (