ወንጌሎች ኢየሱስ ተልእኮውን ለመፈጸም የሚያስችል ስልት እንዳለው ያሳዩናል። በእርሱ የድነት መልእክት ወደ አለም ለመድረስ የዘረጋው ስልት ደቀ መዛሙርቱን የአለምን ፍላጎት እንዲያሟሉ ማሰልጠን እና ማስተማርን ያካትታል። ኢየሱስ ተከታዮቹን በእራሱ እና የእግዚአብሔርን ከተፈጥሮ በላይ የሆነ አቅርቦትን መቀበል በሚያስፈልጋቸው መካከል ስልታዊ በሆነ መንገድ ያስቀምጣቸዋል። ከሙታን የተነሣው፣ የሕያው ክርስቶስ ዕቅድ አሁንም ደቀ መዛሙርቱን መጠቀም ድነት ለሚያስፈልጋቸው የምሥራቹን እውነት ለማድረስ ነው።