እኛ የምንኖረው ውድድር በበዛበት ዓለም ውስጥ ነው፡፡ እንዴት አድርገን ከእኛ “ተወዳዳሪዎች” ወይም ባላጋራዎች ጋር እንደምንኖር የኢየሱስ ትምህርት ግልጽ ያደርገዋል፡፡ የሚያስታርቁ ደቀ መዛሙርት ከጠላቶቻቸው ጋር ችግር ውስጥ መግባት የለባቸውም፡፡ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ግንኙነት ኢየሱስ አስተምሯል፡፡ በእርግጥ እንደ ጨውና እንደ ብርሃን መፍትሄ ለመሆን የወሲብ ፍላጎታችንን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብን መማር አለብን፡፡ እግዚአብሔር ለጋብቻ ፍቺን በፍፁም እንዳላቀደ ኢየሱስ አስተማረ፡፡