በዚህ ትምህርት በጥልቀት የምንመለከተው ነገር የአሥርቱን ትዕዛዛት ዓላማና እያንዳንዱን ትዕዛዝ ሲሆን፣ ኢየሱስ እነዚህን ትዕዛዛት እንዴት እንደተረጎማቸውና በእርሱ ዙሪያ በነበሩ ሰዎች ሕይወት ላይ እንዴት እንደተገበረው ነው፡፡ አሥርቱ ትዕዛዛት የተፃፉት በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ነው፡፡ አራቱ በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል ስላለው ግንኙነት የሚናገሩ ሲሆን፣ ስድስቱ ደግሞ እኛ ከሰዎች ጋር ሊኖረን