የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምዕራፍ ስድስት ስለ እስጢፋኖስ መታሠር፣ እርሱ በስብከቱ በኢየሩሳሌም ለሚገኙ የአይሁድ መሪዎች ብሉይ ኪዳንን ታሪክ አጠቃልሎ በአጭሩ ማቅረቡንና ስለ እርሱ የሰማዕትነት ሞት ይናገራል፡፡ ከእስጢፋኖስ ሞት በኋላ ሁለት አስደናቂ ነገሮች ተከናወኑ፡- ፈሪሣዊው ሳኦል ሐዋርያው ጳውሎስ የተባለው ሕይወቱ ተለወጠ፣ እና እግዚአብሔር ስደቱን በመጠቀም ክርስቲያኖችን ከኢየሩሳሌም ውጭ እንዲበተ