በዳንኤል ዘመን ባቢሎን የልዕለ ኃያሉ የባቢሎን ግዛት ዋና ከተማ ነበረች፡፡ የግዛቱ ንጉሥ ናቡከደነፆር ኃያልና ኩሩ ሰው ነበር፡፡ የናቡከደነፆር መለወጥ እጅግ አስደናቂ ተዓምራት ነው፡፡ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎናውያን እምነት መለወጥ ሲገባቸው፣ ባቢሎናውያን ግን ወደ ዳንኤል አምላክ፣ እውነኛውን አምላክ ወደ ማምለክ ተለወጡ፡፡ ናቡከደነፆር እግዚአብሔር የዚህ ዓለም መንግሥታት ሁሉ ትክክለኛ ገዢ እንደሆነ ተ