Sost kilo

የእውነት እውነት ፥ እወድሻለሁ !


Listen Later

ውብትሽን ከሩቅ ለሚያይ 'ፍዝ' ነው ። ሎሚ እንዳቤዠው ሻይ ፥ ካልቀመሱት የአይን ስህተት ነው ። ይሄን ብዥታ እንደሀቅ ተቀብለው ፥ ይገፉሻል ። ለእኔ ግን ፥ ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ።
ከማታውቂው አገር ብትኮምሪ ፥ የቤትሽ የመጨረሻ ሰካራም ፥ እኔ ነው ምሆነው ። ትተሽ ብታዘምሪ ፥ ጭራ ልጌ አጅባለው ። ለእኔ ? ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ።
በፀጋ ሆነ ቅባት ፥ ብቻ ከአንዱ ሆነሽ ብትነፍቂ ፥ ጥላ ጥለትሽን ይዤ እከተልሻለው ። አንቺ በምታምኚው ፥ እኔ እታነመናለሁ ። ውርስ ሥጋዬ ለስደትሽ ጌተሴማኒ ነው ። ዘመኔን የታነፅኩት ፥ ከሚያሳዱሽ ምስካይ እንድሆን ነው ።
ከሰው አፍ ውለሽ ፥ ከሰው አፍ ብታድሪ ፥ ገመናቸውን በአንቺ አይተው በመላ አገር ብትነውሪ ፥ ኮሶ እንዳገሳቸው ተጨማደው ቢጠየፉሽ ፥ ያን ገላሽን ወደው በያው ገላሽ ቢከሱሽ ... አንችን አስጠግቼ ነውረኛ እሆናለው ። እነርሱ ከገቡበት ገነት ፥ አንቺ የተጣልሽበት ፥ ደይን እመርጣለሁ ።
አንቺ ቀርተሽ ፥ ምን ማቅ ኖሮኝ እቀራለሁ ? አግቧቸውን አንገርግሬ ከአንቺው ጋር እጠፋለሁ ። ጣዕምሽን አውልዬ እኔው ነኝ ማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ፤ ከሰው መጥቶ አይደለም ፤ የእውነት ነው ፥ እወድሻለሁ !
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

Sost kiloBy Leoul Zewelde

  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8

4.8

6 ratings