Sost kilo

የመጨረሻዋ እራት


Listen Later

የተለያየነው የተገናኘን 'ለት ነው ። እንዲህ እልህ ፍቅራችንን ሳይወርስ በፊት አንዳችን የአንዳችን ደቅ ነበርን ። አሁን በነብስም በስጋም ተለያይተናል ። ሰው ስለይ ጎበዝ እንደሆንኩ እነግራት ነበር ። የትናንት እንጥፍጣፊ ውስጤ አላስቀርም ። ክፉንም ደግ ጠጠር እንደሞላው አቁፋዳ እንዲረሳ አድርጌ ከባህር እሰደዋለው ። አሁንም የሆነው እንደዛ ነው ። ታሪካችን እንደተቋጠረ ቁልቁል ሰምጧል ።
ትናንት ሲመሽ እንደሁሌው ጣቶቼን ይዛ አልፀለየችም ። ይልቁን አይኖቼ እስኪከደኑ ጠብቃ የቢጃማዋን መቀነት እየጎተተች ከቤት ወጣች ። አረማመዷ ከመሮጥ ለትንሽ ያዘገመ ነው ። ሻሿ ተፈቶ ከመሬት ሲወድቅ ፤ ፀጉሯ እርቃን ሲወጣ እስከማይሰማት ድረስ ።
ዲናዎቹ ሌቱን ሄደችላቸው እንጂ አንዳቸውም ሊይዟት አልመጡም ። ሙራጅ የሽፍታ ሻሞላ ያላደነውን አያርድምናና እነርሱም አራከሷት ። ቢያንስ ቀርድደው እንዲሰቅሏት ብትለምናቸውም ከመሀከላቸው አንድ ሃባ እዛኝ ሳታገኝ ቀረች ። በእንባ የታጠበ ልመናዋ መኖር እንዳገሸገሻት ያሳብቃል ። ሞት ግን የመጣችበትን መንገድ ያህል ራቃት ።
አማራጭ እንዳጣች ሲገባት ገለባ ነፍሷን እንደተሸከመች ወደቤት ተመለሰች ። ከጀርባዋ ሲያጅቧት የነበሩ ቁራዎች የጣሪያው ቆርቆሮ ላይ ሲያርፉ ጥፍራቸው ይንሰጠሰጣል ። እንዳልሰማት ዱካዋን በወለሉ እያሟሸች በለሁሳስ አንሶላውን ገልባ ገባች ። እግሯ ይቀዘቅዛል ። ገላዋ ውስጥ የገባው ቁር ከሰውነቷ አልፎ ወደ አልጋው ተጋባ ። ልክ ሽፋሽፍቷ ሲገጥም በተራዬ ተነሳሁ ።
የመስኮቱ የግራ መዝጊያ ተበርግዶ ንፋስ ያንሰጠስጠዋል ። የመጋረጃው ዘርፍ ሲውለበለብ የዘለበቱ ጠፍር ከማዕዘኑ ጋር እየተላተመ ይንቋቋል ። ዘላ እንደገባች መልሳ እንዳልዘጋችው ገባኝ ። በድንግዝግዙ ፈዝዤ ደቂቃው ነጎደ ፤ ፅልመቱ ሄዶ አልጎኸም።
" ሰዓትህ ደርሷል " ። በውስጤ ያወራሁት ድምፅ አፌን ትቶ በጆሮዬ ወጣ ። ሹክሹክታዬን እንደሰማሁ ከቆምኩበት ወደ ቡፌው ተራምጄ የመሳቢያውን ሰረገላ እንደደገፍኩ ካራ አሰስኩ ።
ወዲያውን ፈፀምኳት ።
እጄና ክርኔ ላይ የተናጠበው ትኩስ ደም ሳይደርቅ ጨረቃ መግቢያዋን መማሰን ጀምረች ። ፀሐይ ግን ለመውጣት 'ራሱ የወሰነች አትመስልም ። የሰማዩ ውዥንብር የምድሩ ቲያትር ነፀብራቅ ነው ። እጅከፍንጅ የያዘችኝ ቅፅበት በምናልባት ረግታ ለመፍረድ ስታሰላስል ይመስላል ።
ሐሙስ ማታ - መዐድ ቀርባ ስትጠብቀኝ የመጨረሻችን ( የመጨረሻዋ ) እራት እንደሆነ ታውቅ ነበር ። ስትስቅ ግን ለዛዋ እንዳለ ነው ። እንደሁሌም ፈገግታዋን ለማገዝ የአይኖቿ ዳር ይሸበሸባል። በአፍንጫዎቿ ጫፍ የአንገቴን ስር ትታከከኛለች ። ምኗም የተረበሸ አትመስልም ። ነገን እንደማትኖር እያወቀች ስለሚፈሰው ደሟ ፅዋ አልቀዳችልኝም ። አታላኛለች ።
ረጅሙ ሌት ሟጦ እንደምንም አርብ እስከወጋገኑ ጠባ ። ታጥቦ ያልተወለወለ የሣህን ላብ በመሃረቤ አደራርቄ ጠረጴዛው ላይ አኖርኩ ። የመጀመሪዬን ቁርስ ለብቻዬ እያበሰልኩ ነው ። ህልም የሆነ አዳሬ ረዝሞ እንደማይነጋ ፤ ጭንቀት ሰቅዞ እንዳልያዘኝ አሁን እየተነፈስኩ ነው ። መጥበሻውን አንጋልዬ ዘይት ስጨምር በእሳት የጋለ ልቧ መንቶሻቶሽ ጀመረ ። ይቺ ሴትዘመን ፆሜን ልታስገድፈኝ ነው ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

Sost kiloBy Leoul Zewelde

  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8
  • 4.8

4.8

6 ratings