የኢየሱስን ስብዕና ማለትም አምላክነቱንና ሰውነቱን አጉልቶ ስለሚዘግብ የሉቃስ ወንጌል በብዙዎች ዘንድ የተወደደ ነው፡፡ ይህ ወንጌል መሢሁ በርህርሄ ራሱን ከእኛ ጋር እንዳመሳሰለ ያሳየናል፡፡ የጠፋው ልጅና የርህሩሁ ሳምራዊ ዓይነት በርካታ ታዋቂ የኢየሱስ ምሳሌዎች በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ይገኛሉ፡፡ ከሌሎች ወንጌል ፀሐፊዎች በበለጠ ሉቃስ ስለኢየሱስ ልደት በሰፊው ይነግረናል፡፡ በተጨማሪም ሉቃስ የኢየሱ