መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናትና ከህይወታችን ጋር ማዛመድ ሥራን ይጠይቃል፡፡ ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሦስት ክፍሎች ያሉት ሂደት ነው፡፡ እነርሱም፡- ምልከታ፤ ትርጉምና ማዛመድ ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር እነዚህን ሦስት ጥያቄዎች እንጠይቃለን፤ እነርሱም፡ “ምንድነው የሚናገረው?”፣ “ትርጉሙ ምንድነው?” እና “ለእኔ የሚናገገረው ነገር ምንድነው?” የሚሉት ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያው መጽሐፍ