በማቴዎስ 7 ኢየሱስ የእርሱ ደቀ መዛሙርት በሌሎች ላይ እንዳይፈርዱ ያስተምራቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንዲጠይቁ፤ እንዲፈልጉና የእግዚአብሔር አምላካችንን የበጎነቱን መዝጊያንም እንዲያንኳኩ ፤ ሌሎች ለእነርሱ ሊያደርጉላቸው እንደሚፈልጉት እንደዚያው ሁሉ ለሌሎች እንዲያደርጉ ያስተምራቸዋል፡፡ በመጨረሻም የተራራ ላይ ትምህርቱን ሁለት ዓይነት ማለትም ልባም እና ሰነፍ ደቀ መዛሙርትን በማነጻጸር ያጠቃልላል