ዕንባቆም ካህን፣ የአምልኮና የሙዚቃ አገልጋይ ሲሆን እርሱ የኖረው የባቢሎን ወረራ ስጋት ለሁሉም ሰዎች በጣም ግልፅ በሆነበት ጊዜ ነው፡፡ የኢየሩሳሌም ጉበኞች በከተማይቱ መጠበቂያ ማማ ላይ ሆነው ከተማይቱን ሲጠብቁ ዕንባቆም ግን ከእግዚአብሔር ለመስማት በመንፈሳዊ መጠበቂያ ማማ ላይ ነበር፡፡ እርሱ የሚታወቀው በተደጋጋሚ እግዚአብሔርን ለምን በማለት በመጠየቅ ሲሆን የይሁዳ ሰዎች በሙሉ ከሚጠይቁት ጥያቄ ጋ