መዝ 124 ” 1 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል። 2 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥ 3 ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤ 4 በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤ 5 በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር። 6 ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ። 7 ነፍሳችን እንደ ወፍ […]