ዘሪቱ ከበደ በጣም የምወዳት አርቲስት ናት። በቀደመውም ህይወቷ በአሁኑም ህይወቷ የሰራቻቸውን ስራዎች አደንቃለሁ። ጴንጤያዊው ማህበረሰብ "ዘፈንም መዝሙርም እንዴት?" እያለ አንገቷን በሚቀነጥስበት ጊዜም ወገቤን አስሬ ተከራክረታላሁ ቆሜላታለሁ። ያ ማህበረሰብ የራስህን የለውጥ መንገድ process ለመጠበቅ የማይታገስ፣ ሰድቦ አሸማቆ እንድታምንለት እና የራሱ ለማድረግ ይጥራል እንጂ በራስህ conviction ተለውጠህ በጌታ ጊዜ ቤቱን እንድትቀላቀል የማይፈቅድልህ ፈረደኛ ማህበረሰብ ነው። መቼም ዘሪቱ ቲክቶክ ላይ በሚያሽቋልጠው Pente ህዝብ እንደማትሸውድ እርግጠኛ ነኝ።
የኔ ችግር ከዘሪቱ ጋር ይሄ ነው
ለትግራይ ህዝብ ድምጿን ስለነፈገች ፣ ይልቁንም የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖር በትግራይ ጦርነት ህፃናቶች መሳተውፋቸውን ያመላከተች ይህም ስለ ጦርነቱ ካላት የእውቀት መጉደል ፣ የትግራይ ህዝብ ያለበትን መቀመቅ ካለመረዳት፣ ለማወቅ ካለመፈለግ አልያም የመንግስትን መረጃዎች ለማሰተላለፊያ መጠቀሚያ ከመሆን የሚነሳ ስህተት ሰርታለች።
ሁለተኛው ስህተት የትግራይ ሴቶች በሌላ ሃገር ዜጎች እና በብልፅግና ወታደሮች በሚደፈሩበት ጊዜ May 15, 2021 "የሃገር ካስማ" https://www.youtube.com/watch?v=DvaznvrLfkk በሚል ርዕስ የተለቀቀ ሙዚቃ ላይ ከኢትዮጵያዊያን ሴት ዘፋኞች ጋር አደናጋሪ፣ የትግራይን ስቃይ በሚሸፍን መልኩ Distraction በመፍጠር የትግራይ ስቃይ እንዲደበሰበስ ሰርታለች።
ሶስተኛው ለችግን ተከላ የሰጠችውን ትኩረት ያህል ለትግራይ እናቶች ያልጮኸችበትን ምክንያት ስለማልረዳው ፣ የዛን ህዝብ ስቃይ ከፖለቲካ አስተሳሰብዋ ወይንም ከሃይማኖትዋ የተነሳ እንዳይገለጥ ሸፍናለች or ለአብይ ካላት ድጋፍ የተነሳ ሊሆን ይችላል ብዬ ስለማምን።
ዛሬ ላይ ያድናል ብላ የዘመረችለት ኢየሱስ የትግራይን ህዝብን ይጨምራል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ጫረብኝ። ዘሪቱ በትግራይ ጦርነት ለምን በእድሜያቸው ልጆች እንደተሳተፉ ታውቅ ይሆን ዘሪቱ ስለ ሞናሊዛ እና ስለ ቤቲ ሰምታ ይሆን፣ ዘሪቱ ስለ ትግራይ እናቶች መደፈር አታውቅም ይሆን ዘሪቱ ስለትግራይ ህዝቦቼ እና ደሞቼ የምትለው እስከሌላት ድረስ የሚያድነውን እውነተኛውን ኢየሱስን ስለማመኑዋ እጠራጠራለሁ። ነገር ግን "የጴንጤዎችን ኢየሱስ" ግን ልትቀበለው ትችላለች።
የትግራይ ህዝብ መልካም በሚመስሉ፣ ሀይማኖተኛ በሚመስሉ፣ በጎ አድራጊዎች በሚመስሉ ፣ ችግኝ በሚተክሉ ለclimate change የሚጨነቁ በሚመስሉ፣ ሀገር ወዳድ በሚመስሉ ሰዎች ፣ ባለስልጣኖች፣ ኤሊቶች፣ ፖለቲከኞች። ዐርቲስቶች፣ ዘፋኞች፣ ሰባኪዎች ዘማሪዎች ለሞት እንደተዳረገም አንረሳም።
በዘሪቱ ተስፋ የማልቆርጥበት ምክንያት ወደ ውስጥዋ የምታይ ሴት ስለሆነች አንድ ቀን ወደ ልቧ ተመልሳ እንደ ዜጋ ፣ እንደ ሴት፣ እንደ አርቲስት፣ እንደ "ክርስቲያን" የሰራችውን ስህተት በትግራይ ላይ ታየዋለች ብዬ የማምነው ነፍስ ስላላት ነው። በህይወቷ ስትሄድ ስትሄድ፣ ስትፈልግ ስትፈልግ የደረሰችበንት እድገት አይቼ ስለስዋ ግን እግዚአብሔርን አመስግናለሁ።
ጨርሻለሁ።