በአሶሳ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት እየተስተዋለ የሚገኘውን የማንጎ በሽታን ለማከም የተደረገው ጥናት ለውጥ ማስገኘቱን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች አጋሮች ጋር ለሁለት ዓመታት በተደረገው ጥናት በአሶሳ በሁለት ቦታዎች ላይ በሽታውን በማከም ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኒዎሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ዶ/ር አብዱልሙሲን ሀሰን አመልክተዋል፡፡ ጥናቱ አብዛኛውን የገቢ ምንጫቸው በማንጎ ምርት ላይ ያደረጉት አርሶ አደሮችን ችግር እንደሚፈታም አክለዋል፡፡