Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle:How many episodes does በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle have?The podcast currently has 360 episodes available.
November 05, 2025የኤሎን ማስክ ግሮክፒዲያ ምን የተለዬ ነገር ይዞ መጣ?ቱጃሩ ኤሎን ማስክ፤ በቅርቡ ግሮክፔዲያ ተብሎ የሚጠራ በሰውሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረተ አዲስ የበይነመረብ ኢንሳይክሎፔዲያ ይፋ አድርጓል። ግሮክፔዲያ በጎርጎሪያኑ ባለፈው ጥቅምት 27 ቀን 2025 ይፋ የተደገ ሲሆን፤በአሁኑ ጊዜ 900,000 የሚጠጉ መጣጥፎችን በውስጡ ይዟል።ለመሆኑ አዲሱ ዲጅታል መድረክ ከዊኪፒዲያ በምን ይለያል?...more14minPlay
October 29, 2025በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ሀሰተኛ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንዴት እንለይ?በሰውሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የሚፈጠሩ ሀሰተኛ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ባለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው።በተለይ ዲፕፌክ የሚባለው ዘዴ ሰዎች ያልተናገሩትን አስመስለው የሚናገሩ፣ያላደረጉትን ድርጊት የሚፈጽሙ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይውላል። ለመሆኑ እነዚህ ይዘቶች ከእውነተኛዎቹ እንዴት መለየት ይቻላል?...more16minPlay
October 22, 2025የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችከ60 ዓመታት በላይ በአጭር ሞገድ ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ዶቼ ቤለ ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአጭር ሞገድ ሥርጭቱን ያቋርጣል።በምትኩ በሳተላይት እና እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብ እና ቴሌግራምን በመሳሰሉ ዲጅታል መድረኮች ስርጭቱን ይቀጥላል።ያም ሆኖ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ላልሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ውሳኔው የሚጎዳ ነው ተብሏል።...more12minPlay
October 15, 2025የ2025 የኬሚስትሪ እና የፊዚክስ የኖቬል አሸናፊ ግኝቶችየዘንድሮው የኖቬል ሽልማት በኬሚስትሪ ዘርፍ ተፈጥሯዊ የብረት ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ምርምር ላደረጉት ሶስት ሳይንቲስቶች ተሰጥቷል።ይህ ግኝት ብክለትን ለመቀነስ፤በረሃማ በሆኑ አካባቢዎች እርጥበታማ አየርን በመጭመቅ ዝናብ እንዲኖር ለማድረግ፣ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።በፊዚክስ ዘርፍ ደግሞ የኳንተም ሜካኒካል መተላፊያ አሸናፊ ግኝት ሆኗል።...more11minPlay
October 09, 2025ኢትዮጵያ የኒዩክሌር ኃይል ማመንጫ ያስፈልጋታልን?የኑክሌር ኃይል ለአዳጊ ሀገራት ዕድሎችን እና ጉልህ ተግዳሮቶችን አካቶ የያዘ ነው።የኑክሌር ሃይል ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለመደገፍ እና ከካርቦን ነፃ የሆነ አስተማማኝ ኃይል ለማግኘት ይረዳል ። ነገር ግን ማብላያውን ለመገንባት ከፍተኛ ወጭ ይጠይቃል። የሕግ ማዕቀፎችን ፣ ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲሁም ትልቅ እና የተረጋጋ የኤሌክትሪክ መረቦችን ይፈልጋል።...more12minPlay
October 01, 2025የጠፈር ቴክኖሎጂ ለአፍሪቃ ቅንጦት ነውን?ስለ ጠፈር ቴክኖሎጂ ሲነሳ ብዙ ጊዜ የሚታሰበው ስለጨረቃ እና ማርስ ጉዞ ነው። ከዚህ አኳያ ቴክኖሎጂው በድህነት እና በኋላ ቀርነት ስማቸው ተደጋግሞ ለሚነሳው የአፍሪቃ ሀገራት ቅንጦት ተደርጎ ይታያል።እውን የጠፈር ቴክኖሎጂ ለአፍሪቃ ቅንጦት ነውን?...more10minPlay
September 24, 2025የአውሮፓ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ከስራ ያስተጓጎለው የሰሞኑ የሳይበር ጥቃትካለፈው አርብ ምሽት ጀምሮ በአውሮፓ ታላላቅ አውሮፕላን ማረፊያዎች የመንገደኞችን የመግቢያ ፍተሻ የሚከውኑ የዲጅታል ስርዓቶች ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል።በሂትሮው፣በርሊን እና ብራስልስ አየር ማረፊያዎች የደረሰው ይህ የሳይበር ጥቃት በመያዣነት ወይም በ«ራሰምዌር» የተከሰተ ነው ሲል የአውሮፓ ህብረት የሳይበር ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቋል።...more12minPlay
FAQs about በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle:How many episodes does በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle have?The podcast currently has 360 episodes available.