በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle

በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle

Download on the App Store

በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle episodes

  • ብራይት ኬን፤ዓይነስውራንን በድምፅ የሚመራው ቴክኖሎጂ
    ብራይት ኬን የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የፈጠራ ስራ ባልተስተካከሉ መንገዶች እና በተጨናነቁ ጎዳናዎች ላይ እንቅፋቶችን እና አደጋዎችን ቀድሞ ለማስጠንቀቅ ያግዛል።ይህ መሳሪያ የ«አልትራሶኒክ ሴንሰሮች»ን በመጠቀም የተገነዘበውን አደጋ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በድምጽ ያሳውቃል።በዚህም አይነስውራንን ከአደጋ ያስጠነቅቃል አቅጣጫም ይመራል።
    12 min
  • የዲጅታል ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተከታዮቻቸው ላይ ያላቸው አወንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ
    የቲክቶክ፣ ዩቲዩብ እና ኢንስታግራም እና የፌስቡክ ዘመን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ከተዋናዮች፣ ስፖርተኞች ወይም ከፖለቲካ መሪዎች - በተለይም በወጣቶች ዘንድ የበለጠ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው። ነገር ግን የሚያቀርቧቸው ይዘቶች ጠቃሚ እና በሳል ዕይታ እና አስተሳሰብ የታከለበት ካልሆነ፣ተፅዕኗቸው በሚከተሏቸው ወጣቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
    12 min
  • የኦንላይን ግብይት ስጋቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች
    ማሽን ሰዎችን ተክቶ እንዲሰራ የሚያደርገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በዲጅታል መንገድ ግብይቶችን ለመፈፀም አገልግሎት ላይ ይውላል። ቴክኖሎጂው የኦንላይን ግብይቶችን ምቹ እና በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አቅርቦቶችን ለማግኘት የሚያግዝ ቢሆንም፤ የግል መረጃ ደህንነት፣ ማጭበርበር ፣ የቁጥጥር ወይም የግልጽነት ችግር ስጋቶች ናቸው።
    13 min
  • በማንጎ ተክል በሽታ ላይ የተደረገው ምርምር
    በአሶሳ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት እየተስተዋለ የሚገኘውን የማንጎ በሽታን ለማከም የተደረገው ጥናት ለውጥ ማስገኘቱን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች አጋሮች ጋር ለሁለት ዓመታት በተደረገው ጥናት በአሶሳ በሁለት ቦታዎች ላይ በሽታውን በማከም ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኒዎሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ዶ/ር አብዱልሙሲን ሀሰን አመልክተዋል፡፡ ጥናቱ አብዛኛውን የገቢ ምንጫቸው በማንጎ ምርት ላይ ያደረጉት አርሶ አደሮችን ችግር እንደሚፈታም አክለዋል፡፡
    10 min
  • የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለምን አሳሳቢ ሆነ?
    የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ ሰሞኑን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።ኮሚሽነሩ እንዳሉት በተለይም ጀነሬቲቭ ኤአይ ቁጥጥር ካልተደረገበት «ራንከንስታይን ሞንስተር» እየተባለ የሚጠራውን እኩይ ወይም በተለምዶ «ጭራቅ» የምንለው አይነት ገፀባህሪ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
    11 min
  • የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዕድል እና ፈተና በአፍሪቃ
    ሰውሰራሽ አስተውሎት በዓለም ላይ በፍጥነት እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ነው።ቴክኖሎጂው ትምህርትን ግላዊነት በማላበስ፣ በቂ አገልግሎት ለሌላቸው ተማሪዎች ተደራሽነትን በማሻሻል በአፍሪካ በትምህርት ላይ በጎ ተጽእኖ እያሳደረ ነው።ያም ሆኖ ቴክኖሎጂውፈተናዎችም አሉት።ባለሙያዎች ፈተናዎቹን ለመሻገር ቴክኖሎጂው የሚገዛበት ፖሊሲዎች ማውጣትን ይመክራሉ።
    12 min
  • የዓይን ብርሃንን ይመልሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ ቴክኖሎጂ
    የአሜሪካ እና የአውሮፓ ተመራማሪዎች፤ የእስፒል ራስ መጠን ያላት በጣም ትንሽ ቁስ (ቺፕ) ሬቲና በሚባለው የዓይን ክፍል ውስጥ በመቅበር የዓይን ብርሃንን ለመመለስ ያስችላል የተባለ ህክምና ላይ ሙከራ አድርገዋል። በአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ፣ ኔዘርላንድ እና ጣሊያን በተደረገ ሙከራ ተስፋ ሰጪ ውጤት መገኘቱንም ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።
    12 min

About በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle

From the publisher's feed

ሳይንሳዊ እና ስነ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን እና ለህብረተሰቡ ያላቸቸውን ጠቀሜታ ይመለከታል።