ኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት መከተል ከጀመረች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ባንክ ባካሔደው ጨረታ አንድ ዶላር በ107 ብር ከ90 ሣንቲም ተሸጧል። ተመኑ ትላንት በባንኮች ከነበረው አማካኝ ምንዛሪ በ4 ብር ገደማ ከፍ ያለ ነው። ባንኮች በምንዛሪ ተመን ሲሽቀዳደሙ በተለምዶ ጥቁር እየተባለ የሚጠራው የትይዩ ገበያ ተዋንያን አድፍጠው ይታዘባሉ። በአዲሱ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት የዋጋ ግሽበት በጥር ከ30 እስከ 35 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሰነድ ያሳያል።