አፍሪካ በማዕድናት፣ በሚታረስ መሬት እና በኢንዱስትሪ ያላትን እምቅ ሀብት ለዛሬውም ሆነ ለወደፊቱ ትውልድ ሲባል መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር አሳሰቡ። ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ በሚያዝያ 2018 በሚካሔደው የጅቡቲ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ በገደምዳሜ ፍንጭ ሰጡ። በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ማኪና በተባለ አካባቢ በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ የ79 ሰዎች አስከሬኖች ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ሆስፒታሎች መድረሳቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።