በትግራይ ክልል 1,2 ሚልዮን ሕፃናት እና አዳጊ ልጆች ወደ ትምህርት ገበታ አለመመለሳቸው ተገለጸ። ከዚህም ሌላ በክልሉ የትምህርት ጥራት ላይም ክፍተት መኖሩ ተጠቁሟል።
በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት የኢትዮጵያ ማህበር አንድ አመራር አባል መገደላቸውን የሟች የሥራ ባልደረቦች እና ቤተሰቦች ገለጹ።
በናይጀሪያዋ ፕላቶ ግዛት ውስጥ ታጣቂዎች ለቀናት ባደረሱት ጥቃት 52 ሰዎችን ገደሉ። ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎችም ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቀሉ።
የአውሮጳ ሕብረት የትራምፕ አስተዳደር የጣለውን አዲሱን ቀረጥ በተመለከተ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።