Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
September 09የጳጉሜ 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና-- የአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸዉ የኢሕአፓ መሪዎችና ጠበቃ በዋስ እንዲፈቱ የተላለፈላቸዉ ዉሳኔ ታገደ።-ብሪታንያ ምሥራቃዊ እየሩሳሌም ዉስጥ የሚገኝ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቷን እንድትዘጋ እስራኤል ማሳሰቧን ብሪታንያ የሚጠበቅ፣ግን አሳዛኝና ግንኙነትን የሚያበላሽ በማለት ነቀፈችዉ።-የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።13 minPlay
September 08የዓለም ዜና፤ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞአርስተ ዜና፤ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች ሞቱ። -በትግራይ ክልል የሚገኙ አማፅያን የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ ሌላ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል አሉ።-በሌላ በኩል በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ የወጣቶችና የታዳጊ ልጆች አፈሳ ይቁም ሲሉ በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ እናቶች ለተቃዉሞ ወጡ።13 minPlay
September 07የጳጉሜ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜናየትግራይ ክልል ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ “ገለልተኛ አይደሉም” በማለት ወነጀለ። በኢትዮጵያ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጥሪ አቀረቡ። መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ያስመዘገው የምርጫ ድል ፓርቲያቸውን ከመሠረቱ እንደነቀነቀ ተናገሩ12 minPlay
September 06የጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜናበየመን መንግስት ኃይሎችና «በኢራን ይደገፋሉ» የሚባሉት የሑቲ ደፈጣ ተዋጊዎች መካከል ትላንት አገርሽቶ እስከ ዛሬ በተካሄደ ውግያ ከሁለቱም ወገን ከ140 በላይ ወታደሮች መገደላቸውን ተሰማ። በምሥራቅ ጀርመን በምትገኘው የዛክሰን አንሃልት ግዛት የአካባቢ ምርጫ እየተካሄደ ነው።9 minPlay
September 05የነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና• በደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ምስራቅ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 20 ሰዎች ተገደሉ ። አስራ ስድስቱ የመንግስት ወታደሮች እና ፖሊሶች ናቸው ። • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ።12 minPlay
September 04የነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜናበኢትዮጵያ በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራ ለማቋቋም ወደ 38,000 ኮምፒውተሮች እንደሚያስፈልግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ።12 minPlay
September 03የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜናበወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሾመው የሱዳን ጉዳይ የምርመራ ቡድን፤ የውጭ ሐገራት ታጣቂዎች በሐገሪቱ ያለውን ግጭት እያባባሱት ነው ሲል ከሰሰ። የእስራኤል ጦር አባላት በምዕራባዊ ዮርዳኖስ የባሕር ዳርቻ 2 ፍልስጤማውያን ወጣቶችን ተኩሰው መግደላቸውን11 minPlay
September 02የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዓለም ዜና-የጀርመንና የሩሲያ ተዘዋዋሪ ግጭት ወደ ቀጥታ ዉዝግብ፣ የጥቃት ሙከራ፣ ቅጣትና የአፀፋ ቅጣት ዛቻ ንሯል።---የቻይና መሪ ሺ ጂፒንግ የዉጪ መንግሥታት በመካከለኛዉ ምሥራቅ የዉስጥ ጉዳይ ጠልቃ እንዲገቡ የአካባቢዉ መንግሥታት መፍቀድ የለባቸዉም አሉ።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን አንዳቸዉ የሌላቸዉን ተቋማትና ጥቅሞች መደብደባቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።12 minPlay
September 01የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜናአርዕስተ ዜና የኬንያ የአቪዬሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማቸውን ማቋረጣቸው ተገለፀ ። የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀካይንዴ ሂቺሌማ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ ። የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ላይ ለያዘችው አቋም ፑቲንን አመሰገኑ። ፑቲንም ፔሽኬቭያንን ለተጋድሎአቸው አወደሱ12 minPlay
August 31DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 የዓለም ዜናበአንድ ሣምንት 2,463 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት ከ6,000 በላይ ሰዎች በኢቦላ መያዛቸውን አረጋገጠ። በሱዳን የታቀደው ብሔራዊ ውይይት “የመጨረሻ ግብ በሕጋዊ ሲቪል ተቋማት የምትመራ፣ አንድ ወጥ ብሔራዊ የጸጥታ መዋቅር” ያላት “የተባበረች፣ ሉዓላዊ እና ሰላማዊ” አገር መፍጠር ሊሆን እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን መከረ። ሕንድ ከፓኪስታን ጋር የተፈራረመችውን የውኃ መጋራት ሥምምነት እንድታከብር በፍርድ ቤት የተላለፈባትን ውሳኔ ውድቅ አደረገች። የአሜሪካና ኢራን ጦርነት ዳግም ሲያገረሽ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ።12 minPlay