የሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
ሳዑዲ አረቢያ 2 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች። የሳዑዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለቱ የኢትዮጵያ ዜጎች በሞት የተቀጡት አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር ተከሰው መሆኑን ትናንት መናገሩን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።ኢትዮጵያውያኑ ሀሽሽ የተባለውን አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለዋል ።
ከጎርጎሮሳዊው ግንቦት መጨረሻ ወዲህ በጋዛ እርዳታ ለማግኘት ከሞከሩ ሰዎች ወደ 800 የሚጠጉት እንደተገደሉ የተመድ ዛሬ አስታወቀ።
አሜሪካን በተመድ ድርጅት ልዩ ባለሞያ ላይ ማዕቀቦች ለመጣል መወሰኗ ክፉኛ እንዳሳዘነው የአውሮጳ ኅብረት ዛሬ አስታወቀ።