የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕሰተ ዜና
    -በምሥራቃዊ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ የተቀሰቀሰው በግንቦት የመጀመሪያ ሣምንት ከመታወጁ ሦስት ወራት ገደማ አስቀድሞ እንደነበር የዓለም የጤና ድርጅት ዛሬ አስታወቀ።
    -ዩክሬን በሩስያ ላይ በጣለችው የድሮን ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ 13 ሰዎች መገደላቸውን 39 ደግሞ መቁሰላቸውን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ።
    -ኮሎምብያና ጎረቤቶቿን የላቲን አሜሪካ ሀገራት በመታው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 18 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። የርዕደ መሬት ንዝረት እስከ ኢኳዶር፣ ፓናማ እና ቬንዙዌላ ድረስ ተሰምቷል።
    12 min
  • የነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስቱ እና የክልል መሪዎች እውነተኛ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ጥሪ አቀረቡ ።
    • በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማፂያን በሳውዲ አረቢያ የቀይ ባሕር ዳርቻ በሚገኘው የነዳጅ ማጣሪያ ላይ በድሮን ጥቃት ማድረሳቸውን አስታወቁ።
    • የሮማ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሱዳናዉያን የሰብአዊ ርዳታ የሚያልፍባቸው መስመሮች በአስቸኳይ እንዲከፈቱ ጥሪ አቀረቡ።
    • አሜሪካ ኦሬገን እያስተናገደች ባለው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጡ።
    9 min
  • የነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና በአለታ ወንዶ ከተማ በመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ከ178,000 በላይ ስደተኞች ከደቡብ አፍሪቃ መልቀቃቸውን፣ኢራን እና ኦማን ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል ማለታቸውን፣ኢራን በኤምሬትስ መርከብ ላይ ጥቃት ፈፀመች መባሉን፣በጀርመን ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ድሮኖች መታየታቸውን ፣እንዲሁምየአውሮፓ ህብረት የአውሮፓ ህብረት በሴውታ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ላይ ከትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር መምከሩን አካቷል።
    12 min
  • የነሐሴ 1 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መንግሥት ሐገርና ሕዝብ ጎድተዋል፣ ገንዘብ አጭበርብረዋል፣ በሙስና ተዘፍቀዋል ያላቸዉን ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ማሰሩን አስታወቀ።----የዩጋንዳ ጦር የጋዛን ሠላም ለማስከበር ይሰፍራል ለተባለዉ ዓለም አቀፍ ሠራዊት ወታደሮች እንዲያዋጣ የሐገሪቱ ምክር ቤት ወሰነ።የጋዛን ሠላም ያስከብራል የተባለዉ ዓለም አቀፍ ሠራዊት የሚሰፍርበት ጊዜ በዉል እይታወቅም።--ሳዑዲ አረቢያ፣ ቱርክና ፓኪስታን የጦር ቃል ኪዳን ሥምምነት ተፈራረሙ።የሶስቱ ሐገራት መሪዎች ዛሬ መካ-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በተፈራረሙት ሥምምነት መሠረት አንዱ ሐገር ከተጠቃ ሶስቱም እንደተጠቁ ይቆጠራል።
    13 min
  • የሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለተጨማሪ ዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት መቀጠሉን የተለያዩ ወገኖች አስታወቁ።
    ከራያ አለማጣና አካባቢው በጦርነት ስጋት ከተፈናቀሉ ሴቶች መካከል በርካቶቹ ለአሰቃቂ የቡድን ጾታዊ ጥቃት፣ ለአካል ጉዳትና ለሕክምና እጦት ችግር መዳረጋቸውን አስታወቁ። የህክምና ባለሞያ ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑት ሴቶች ከለላ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
    የአዲስ ስታንዳርድ ባለቤት Jakenn Publishing Plc እንዳስታወቀዉ ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር በመንግሥት የሥለላ ኃይላት ከመታገቱ በተጨማሪ ተደብድቧል፤ ተንገላትቷል፤ ታስሯልም።
    11 min
  • የሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን በሚገኙ አምስት ወረዳዎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት የተለያዩ ሰብሎችና አትክልቶችን ለጉዳት መዳረጉን ነዋሪዎች እና የዞኑ አስተዳደር ለዶቼቬለ ተናገሩ።
    በዴሞክራቲክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ግዛት የተቀሰቀሰው የኢቦላ ተሐዋሲ ስርጭት መባባሱ ተገለጸ። የሟቾች ቁጥር ከ1,700 በልጧል።
    በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጽያን በአንድ ተጨማሪ የሳዑዲ አረብያ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸመቸው ተዘገበ።
    ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭና አካባቢው ላይ በሚሳኤል እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 17 ሰዎች ተገደሉ፤ ከ40 በላይም ቆሰሉ።
    10 min
  • የሐምሌ 28 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነዉ የሴቲት ወንዝ ዉስጥ 15 የትግራይ ተዋጊዎች አስከሬን መገኘቱን የሱዳን የሕክምና ባለሙያዎች አስታወቁ።የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና የህወሓት ተዋጊዎች አዲስ የገጠሙት ዉጊያና የዉጊያ ዝግጅት ሰላማዊ ሰዎችን ለከፋ አደጋ እንደሚያጋልጥ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስጠነቀቀ።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የሚያደርጉት ድርድር አግባቢ ዉጤት እያሳየ መሆኑን አደራዳሪዎችና የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ።-የእስራኤል ጦር የዛሬ ሶስት ዓመት ግድም ጋዛ ከተማ ዉስጥ በጅምላ የገደላቸዉ 112 ፍልስጤማዉያን ዛሬ በጅምላ ተቀበሩ።
    12 min
  • የሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ-ዜና
    በራያ አላማጣ ግንባር ወታደራዊ ፍጥጫ እና የጦርነት ዝግጅት ማየሉን ነዋሪዎች ገለጹ። በአካባቢው ፣ ቤት ለቤት ዝርፊያ መስፋፋቱን የትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎት በመስተጓጐሉ ደንበኞች ለተጨማሪ ክፍያ መዳረጋቸውንም ተናግረዋል
    በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጦርነት ሸሽተው ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን እየገቡ ነው ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘገበ። ከመካከላቸው ቁስለኛ ተዋጊዎች ይገኙበታል
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚካሄደውን ጦርነት ከፍጻሜ ለማድረስ ዛሬ ሰኞ ድርድር ይጀመራል ሲሉ ቴህራን ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ድርድር እያካሄድኩ አይደለም ብላለች
    13 min
  • የሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    በመከላከያ ሠራዊትና በትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ሸረሪና በተባለ ቦታ የተጀመረው ውጊያ መቆሙን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ፈጸመችው በተባለ የአየር ጥቃት 15 ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማስቆም በአፋጣኝ ስምምነት ላይ ከተደረሰ ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ላለመሰንዘር መስማማታቸውን ገለጹ። በኢንዶኔዥያ በአንዲት ጀልባ በደረሰ የእሳት አደጋ 5 ተሳፋሪዎች ሞተው 41 የደረሱበት አለመታወቁን የሐገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
    9 min
  • የሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና ፤በትግራይ አዲስ ጦርነት መከፈቱን የትግራይ ቴሌቪዥን መዘገቡን፣በሲውታ፤ ስፔን እና ሞሮኮ የድንበር በተከሰተው የስደተኞች ቀውስ የሟቾች ቁጥር 67መድረሱን፣በስፔኗ ሲኡታ ግዛት የሚፈልሱ ስደተኞችን በተመለከተ ውይይት እንዲደረግ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ጥሪ ማቅረባቸውን፣ሁቲዎች የሳውዲ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች የጉዞ መስመር እንዲቀይሩ ማድረጋቸውን፣እስራኤል በፈፀመችው ጥቃት በጋዛ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖችን መውደማቸው መገለፁን እንዲሁም ኢራን አሜሪካን እንዳያግዙ የአካባቢውን መንግስታትን ማስጠንቀቋን አካቷል።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…