የሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ ማለቁንና የፊታችን መስከረም በይፋ ሊመረቅ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዛሬ ተናግረዋል።
የእስራኤል ኃይሎች ዛሬ በጋዛ ባካሄዱት ድብደባ ቢያንስ 69 ሰዎች ተገድለዋል ሲል የጋዛ የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ አስታወቀ። እንደ ኤጀንሲው 5ቱ በአንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ ተጠልለው የነበሩ የጋዛው ጦርነት ተፈናቃዮች ናቸው። ከሞቱት ውስጥ እርዳታ በመጠበቅ ላይ የነበሩ 38 ሰዎችም ይገኙበታል።
የሩስያ ባህር ኃይል ምክትል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ሚኻኤል ጉዳኮቭ ከዩክሬን ጋር በተካሄደ ውጊያ ረቡዕ ተገደሉ።