አርስተ ዜና፤
--ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሩስያዉ ፕሬዚዳንት ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ "ፑቲን ከዩክሪን ጋር የጀመረዉን ጦርነት የማቆም ፍላጎት የለዉም አሉ"። ሩሲያ 550 ድሮን እና ሚሳኤሎችን ተጠቅማ ዩክሬይን ላይ ከፍተኛ የተባለ ድብደባ ፈጽማለች።
--የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ በህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የሱዳን፣ የግብፅና የሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሐገራት መሪዎች እንዲገኙ ያቀረቡትን ግብዣ ግብፅ ዉድቅ አደረገችዉ።
--የፍልስጤሙ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ሃማስ ከእስራኤል ጋር ጋዛ ላይ የሚያካሂደዉን ጦርነት በተመለከተ አንድ የስምምነት ሐሳብ ላይ ለመድረስ ከሌሎች የፍልስጤም ቡድኖች ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።