የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    የዛምቢያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሐገር ክህደት ወንጀል እንደተከሰሱ የሐገሪቱ አቃቤ ሕግ አስታወቀ። በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ በወታደሮች ተቀስቅሶ የነበረው ዓመጽ በኒጀር መንግስት ታማኝ ወታደሮችና በሐገሪቱ ያሉ የሩስያ የአፍሪካ ጓድ ጦር አባላት ድጋፍ መክሸፉን ተከትሎ ከተማዋ በዛሬው ዕለት አንጻራዊ ሰላም ማግኘቷን ተነገረ። እስራኤል በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ ፈጸመችው በተባለ የአየር ጥቃት 2 ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ምንጮች አስታወቁ። ቱርክ፣ ሳውዲ ዓረቢያና ፓኪስታን በጋራ የመከላከያ ስምምነት ላይ ለመምከር ነገ በኢስታምቡል እንደሚገናኙ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
    9 min
  • የነሐሴ 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ በደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉበትን ጥቃት አወገዙ። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ “በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ” ያላቸውን 32 ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ አስታወቀ። ሩሲያ ከኪየቭ አቅራቢያ በሚገኝ መጋዘን ላይ በድሮን በፈጸመችው ጥቃት 37 ሰዎች መገደላቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት ገለጹ። ኔፓልና ቲቤት በሚዋሰኑበት ተራራማ አካባቢ በደረሰው የደራሽ ጎርፍ አደጋ መሞታቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 682 ደረሰ።
    11 min
  • የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና ፤የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለስድስት ወራት ተቋርጦ የነበረውን የሮይተርስ ቋሚ የዜና ወኪል ዘጋቢዎች የሥራ ፈቃድ ማደሱን መግለፁን ፣በደቡብ ሱዳን 49 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ባለስልጣናት መግለፃቸውን፣ኤስዋቲኒ አወዛጋቢ በሆነ የሶስተኛ ሀገር ስምምነት መሰረት ሁለት ስደተኞችን ከአሜሪካ መቀበሏን፣በሟቹ የኖሮዌ ንጉስ ሀኖርድ አምስተኛ ምትክ ልጃቸው ንጉሥ ሃኮን ስምንተኛ ተብለው መሰየማቸውን ፣ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ በሩ ጨርሶ አለመዘጋቱን መግለጿን እንዲሁም በኔፓል በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ ከ300 በላይ ህንዳውያን የደረሱበት አለመታወቁን አካቷል።
    14 min
  • የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ሐሙስ
    አርስተ ዜና፤ -በያዝነዉ ነሐሴ ወር ብቻ ከ 60 በላይ ኢትዮጵያዉያን ፤ ከዕፅ ዝዉዉር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ከሳዉዲ አረብያ የሚወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። -በኔፓል እና በቲቤት ድንበር አካባቢ በተከሰተው አውዳሚ ድንገተኛ የጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ 300 በላይ ደረሰ። ከ 1300 በላይ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አይታወቅም።-የአሜሪካው 9/11 ወይም የመስከረም 11 ዱ የሽብር ጥቃት ዋና አቀናባሪ ተጠርጣሪ ካሊድ ሼክ መሐመድ ከ20 ዓመት እስራት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፍርድ ሊቀርብ መሆኑ ተሰማ።-የበቦስኒያ የጦር ወንጀለኛ ጄኔራል ራትኮ ምላዲች በ 84 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
    13 min
  • የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና የኦባሳንጆን የሰሞኑን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለፁን፣በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በትኩረት እና በስጋት እየተመለከቱት መሆኑን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የምዕራባዉያን ዲፕሎማቶች ማስታወቃቸውን፣የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ከስልጣን መልቀቃቸውን፣አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ የጣለችው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ምንም አይነት ግብ አያሳካም ሲሉ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መናገራቸውን፣የአሜሪካ የስለላ ኃላፊ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር መወያየታቸው ን እንዲሁም በጀርመን አንድ የፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ ሰራተኛ በወባ ህይወቱ ማለፉን አካቷል።
    11 min
  • የነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ደቡብ ሱዳን ፤ ሁለት ኢትዮጵያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ። የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ የመቀሌ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ። ኢትዮጵያ እ.ጎ.አ. በ2028 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ሰነዷን በይፋ አቀረበች። የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች 79 ስደተኞችን ታደጉ። ዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልትመልስ ነው። 1501ኛው የመውሊድ በዓል ዛሬ ተከበረ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
    አርስተ ዜና፤ በጫካ የሚገኙትና የፋኖ ንቅናቄ ተራ አባል ነኝ ሲሉ የገለፁልን አቶ እስክንድር ነጋ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከበርካታ የግድያ ሙከራ ማምለጣቸዉን ተናገሩ። እስክንድር ነጋ ጽምዶ የተባለዉን ጥምረት ን የኢትዮጵያ ጠላት ብለዉታል።-ዛሬ 35 ኛ ዓመት የነጻነት ቀንዋን ዛሬ ያከበረች ዩክሬይን መዲናዋ ላይ አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃምን ጨምሮ የአዉሮጳ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።- በመካከለኛው ምስራቅ የቀጠለዉን ግጭት ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ፤ የአሜሪካን ከኢራን ጋር ስላለው ግጭት መፍትሄ ለማግኘት ከቴህራን ጋር በአክብሮት መነጋገር እንዳለባት አጽኖት ሰጡ።
    11 min
  • የነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በደቡባዊ ቱኒዚያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስደተኞችን አፍኖ ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሰጥሞ የስምንት ሰዎች ሕይወት አለፈ።
    • በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት ቦርጉ ግዛት ታጣቂ ጂሃዲስቶች ትክክለኛውን የእስልምና አስተምሮ አልተከተሉም ባሏቸው ምዕመናን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ።
    • ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል የሚያስፈልጋትን የ30 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮጳ ህብረት እንደምትጠብቅ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ።
    • አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ።
    9 min
  • የነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና ከአንድ ወር በላይ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቁን ፣በናይጄሪያ በአክራሪ ቡድኖች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና መታፈናቸው መገለፁን፣የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሃን ዋዴፉል ለጉብኝት ዛሬ ዩክሬን መግባታቸውን፣የስዊድን ፖሊስ በአሥራዎቹ ዕድሜ የምትገኝ ልጅ ትምህርት ቤት ውስጥ መገደሏን ተከትሎ የበይነመረብ ትስስር መድረኮችን እየመረመረ መሆኑን ፣እንዲሁም በምስራቅ ስፔን በተከሰተ የሰደድ እሳት ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸውን አካቷል።
    12 min
  • የነሐሴ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አንጎት፥ መንገድ ዳር የተጠመደ ፈንጂ ባለሦስት እግር ባጃጅ አጉኖ ጉዳት አደረሰ፤ ኦባሳንጆ ከአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ፤ አ.አ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ የማቅረቡ ምክንያት፤ ቡኒያ፥ ኢቦላ ዳግም ከተቀሰቀሰ 100ኛ ቀኑ ተቆጠረ፤ ፓሪስ፥ «ዩክሬንን ለመደገፍ የፈቃደኞች ጥምረት» የተባለው ቡድን ሰኞ ሊሰበሰብ ነው፤ ስቶኮህልም፥ ትምህርት ቤት በደረሰ የጎራዴ ጥቃት በርካቶች ቆሰሉ
    13 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…